RSS

የፊደል ገበታ . . . !

10 Nov

__ ሀ፣ ለ፣ ሐ፣ መ . . . 
ያየሽ አይኔ ታመመ
ልቤም ሲያስብሽ ደከመ
እግሬም ወዳንቺ አዘገመ . . . !

__ ሠ፣ ረ፣ ሰ፣ ሸ . . .
ህልሜ በህልምሽ ታሸ
አቅሜና ልኬ ተፈተሸ

ወኔዬም ጥሎኝ ሸሸ . . . !

__ ቀ፣ በ፣ ተ፣ ቸ . . .
ሩሕሽ ሩሔ ላይ ተምቧቸ
ኑሮዬ በስምሽ ተመቸ 
ህይወት ያላንቺ ሰለቸ . . . !

__ ኅ፣ ነ፣ አ፣ ኘ . . . *
ከቃልሽ ፍስሃ ተገኘ
ከገፅሽ ብርሃን ናኘ
የመውደድ ቅኔ ተቀኘ . . . !

__ ኸ፣ ወ፣ ዐ፣ ከ . . . **
ኑሮና ፍቅር ተቦተለከ 
ድርና ግብር ተሰከሰከ
ነፍሴም ስላንቺ ተብሰከሰከ . . . !

__ ዘ፣ ዠ፣ የ፣ ደ . . .
ብልሃት ከመብላት ተዛመደ
ልኬት ከስኬት ተዋሃደ
ጥፋት ወ ክፋት ተማገደ . . . ! 

__ ጀ፣ ገ፣ ጠ፣ ጨ . . .
ደሜና ደምሽ ካንድ መነጨ
የሕላዌን ቃል በጋራ ረጨ
በዘልዓለም ጥግ ኪዳን ተቋጨ . . . ! 

__ ጰ፣ ጸ፣ ፐ፣ ፈ . . . *** 
ዘመን በዘመን ተተካ አለፈ
ውበትና ጉልበት እያደር ረገፈ

ፍቅሬ ፍቅርሽ ግን
__ ከሰማየ ሰማይ ከአፅናፍ አለፈ::

__________ / © አብዲ ሰዒድ / _________

ትክክለኛው የፊደል አቀማመጥ
* ኅ፣ ነ፣ ኘ፣ አ
** ከ፣ ኸ፣ ወ፣ ዐ
*** ጰ፣ ጸ፣ ፀ፣ ፈ፣ ፐ እና ቨ
 
Leave a comment

Posted by on November 10, 2012 in ግጥም

 

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s

 
%d bloggers like this: