ከግፍና ከመከራ
__ አገር ነፃ ልታወጣ፣
ፍትህና እኩልነት
__ በወገን ደጅ ልታሰጣ፣
ድንቁርናን ልታጠፋ፣
የ’ውቀት ብርሃን ልታሰፋ . . .
ሌት ተቀን የምትዳክር
__ አንተ ቆራጥ ወገኔ፤
ለውለታህ ቃልም የለኝ
__ ብርታት ይብዛልህ ወኔ . . .
ለውለታህ ቃልም የለኝ
__ ብርታት ይብዛልህ ወኔ . . .
*
እቅድ ውጥንህ ተሳክቶ
የልፋትህ ጥግ ፍሬ አፍርቶ
ጨለማችን ለብሶ ትቢያ
ብርሃን ፀዳል ነግሶ ግልቢያ
እንድናየው ባገር ሸንጎ
በደላችን ተጠራርጎ
ጭንቃችንን ተሸክመህ አደባባይ ስትወጣ
ቅንጣት ተስፋችንን ባንደበትህ እንዳናጣ
ከኛ ነፃነት በፊት ነፍስያህን ነፃ አውጣ !!!
(© አብዲ ሰዒድ፣ ሐምሌ 2004 E.C)