ሰላም
የተሰማንን እንተነፍሰው ዘንድ ሰዋዊ ተፈጥሯችን ግድ ይለናል!… የስጋ እርምጃችን በደስታ እንዲሞላ የነፍስ ምግባችንን ቀናነት ብናደርገው መልካም ነው!… ቀና አእምሮ ከ’ሬት ማር ሊያወጣ ይቻለዋልና!… አረረም መረረም እንዳሰብነው እንፅፋለን!… እንደፃፍነውም እናስባለን!… ሁሌም ሰላም!…. ሁሌም ፍቅር!… ሁሌም ቀናነት ከሁላችን ጋር ይሁን!…
ቀና ቀኖች በእጃችን እስካሉ ድረስ የተሰሙንን፣ የገጠሙንን፣ የታዘብነውን እንዲሁም ያነበብናቸውን ነገሮች በቀና ልቦና እንካፈላቸዋለን!… ኢንሻአላህ!
(አብዲ ሰዒድ፣ ጥቅምት 2005 E.C)